በቅርቡ አሜሪካ ባስተላለፈችው የታሪፍ ማሻሻያ መሰረት ኢትዮጵያ ምን አይነት ስራዎች ይጠበቁባታል የሚለዉን መናኸሪያ ሬዲዮ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡
ኢትዮጵያ ላይ የንግድ ታሪፉ ተፅዕኖ ከመፍጠሩ በፊት ሌሎች አማራጭ የገበያ መዳረሻዎችን ማስፋት እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የንግድ ስርዓትን ማሳደግ ላይ ልትሰራ ይገባል ሲሉ የገለፁት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ሞላ አለማየሁ ናቸው፡፡
እንዲሁም መሰል አሁን ላይ የተጣለውን የታሪፍ ጭማሪም ሆነ ከዚህ በኋላ የሚጣሉ ታሪፎችን ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ፖሊሲ በማውጣት እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቦችን በማምጣት በኩል ቀድሞ መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡
ሌላኛው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በረኸተስፋ እንዳነሱት ሀገሪትዋ ያላትን ምርቶች ለውጪ ገበያ የሚያቀርቡ ላኪዎችን በማበረታት ብሎም እሴት እየጨመሩ እንዲልኩ በማድረግ በውጭ ገበያ ላይ ተፈላጊነታቸዉ እንዲጨመር ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ከውጪ የምናስገባቸው ምርቶችን ለመቀነስ ለአምራች ኢንደስተሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
ባለሙያዎቹ የንግድ ማህበረስቡ ከመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ወቅቱ የሚጠይቀዉን አይነት ማሻሺያ ማድረግ እንደሚገባቸዉ ጠቁመዋል፡፡
__
ምላሽ ይስጡ