አለም አቀፉ የወባ ቀን የፊታችን ሚያዝያ 17 ቀን 2017 በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኹነቶች እንደሚከበር በተገለጸበት የጤና ሚኒስቴር መግለጫ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደረጄ ዱጉማ “አዳዲስ ፈጠራዎችንና ሀብትን በማቀናጀት በሁሉ አቀፍ ቁርጠኝነት ወባን እንግታ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበርና አዳዲስ ምርምሮችም ይፋ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ስምንት ወራት 20 ሚሊዮን ዜጎች የወባ ምርመራ እንደተደረገላቸውም የተገለፀ ሲሆን ምርመራውን ካገኙ ዜጎች ውስጥ 8.2 ሚሊዮን የሚሆኑት በሽታው በደማቸው መገኘቱን ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያ የበሽታውን ስርጭት መከላከል የሚያስችሉ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ቤቶች የኬሚካል ርጭት ተደርጎላቸዋል ተብሏል።
ምላሽ ይስጡ