በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 2747 ወንዶች እና 508 ሴቶች፣ 30 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 159 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ መጋቢት 3 ጀምሮ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፤ በዚህም እስካሁን 18 ሺህ 969 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ