👉የቃሉ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ከኮምቦልቻ ቁጥር 2 እስከ ኮምቦልቻ ቁጥር 1 በተዘረጋ 132 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ የኤሌክትሪክ ታወር ላይ ስርቆት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
ሚያዚያ 07 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቃሉ ወረዳ 07 ቀበሌ ልዩ ቦታው ቀዲዳ በተባለ ቦታ 132 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ የኤሌክትሪክ ታወር በመፍታት ለቆራልዮ በመሸጥ በኮምቦልቻ፣ ደሴ ከተሞችን እና በ5 አጎራባች ወረዳዎች፤ ከአቀስታ ኃይል ማካፋፈያ ጣቢያ ሃይል በሚያገኙ የምዕራብ ወሎ ወረዳዎች እንዲሁም ከአለም ከተማ ኃይል ማካፋፈያ ጣቢያ ሃይል በሚያገኙ ከፊል ሰሜን ሸዋ እና አካባቢዎቻቸው ላይ ኤሌክትሪክ እንዲጠፍ ምክንያት የሆኑ 4 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፓሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
የወረዳው ፓሊስ ጽ/ቤት ሃላፊ ኮማንደር ሙሉጌታ በለጠ እንደተናገሩት ፓሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ጥብቅ ክትትል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃላል ተሸካሚ ታወር ላይ ስርቆት በመፈጸም የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረግ ህዝቡ እንዲቸገር ያደረጉ 4 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል።
ሁለቱ በስርቆት ሲሳተፉ ፣ አንዱ ገዥ እና አንዱ በባጃጅ አመላላሽ በመሆን የተጠረጠሩ መሆናቸውን ሃላፊው ገልጸዋል።
ፓሊስ በጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ መጀመሩንና በፍ/ቤት ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ሃላፊው መናገራቸውን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 radio 99.1
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ