ሚያዚያ 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመጪው የትንሳኤ በዓል በዋናው እና በአቃቂ ቅርንጫፍ የቄራዎች ድርጅት ከ6ሺሕ 500 በላይ እንስሳት ለእርድ ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጿል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት መጪውን የትንሳኤ በዓል አስመልክቶ ከ4ሺ በላይ የዳልጋ ከብት እና ከ2ሺ 500 በላይ በግና ፍየል ለእርድ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገ/ሚካኤል ያስታወቁት።
ለበዓሉ ስራ ከ1ሺሕ በላይ ከሚሆኑት የተቋሙ መደበኛ ሠራተኞች በተጨማሪ ለ260 ጊዜያዊ ሠራተኞች ቅጥር መፈጸሙን አስታውቀዋል፡፡
ለባለሙያዎቹ የጤና ምርመራ መደረጉን የገለጹት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው፤ ለአጠቃላይ ሠራተኞች የሞያ ስልጠና እንደተሰጣቸውም አስታውቀዋል፡፡
የእርድ ክፍሎች እድሳትን ጨምሮ የማስፋፊያ ስራዎች መሰራታቸውንም ተናግረዋል፡፡
ለዘንድሮ በዓል የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን እና እርድ ከተከናወነ በኋላም ምርቱን ለማከፋፈል 40 ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 radio 99.1
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ