ነገ ሁለተኛ ዓመቱን የሚይዘው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ12 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያፈናቀለ ሲሆን የዓለማችንን አስከፊ የረሀብ አደጋም ደቅኖባቸዋል፡፡
አሁን ደግሞ በምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍል ኤል ፋሽራ አካባቢ የሚገኘው ዘምዘም መጠለያ ላይ የተቀሰቀሰው አዲስ ጦርነት ሦስተኛ ቀኑን እንደያዘ የሚገልጹት በስጋት ውስጥ ያሉ ስደተኞች ናቸው፡፡
እስካሁንም ሕጻናትና የሕክምና ባለሞያዎችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በርካቶችም ስጋት ውስጥ ገብተዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዳርፉር ባለፈው ሳምንት የተጀመረው ጥቃት በርካቶችን እንደገደለና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ስጋት ውስጥ እንደከተተ ነው የገለጸው፡፡
በአል-ፋሸር ከተማ አቅራቢያ የሚገኙት ዘምዘምና አቡ ሾክ የስደተኞች መጠለያዎች 700 ሺህ ለሚደርሱ ተፈናቃዮች ጊዜያዊ ቤቶች ያዘጋጁ ቢሆንም አብዛኞቹ በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ እንደሆኑ ነው ያስታወቁት፡፡
በመጠለያው ያለውን ሁኔታ የገለጹት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ክሌመንቲን ሳላሚ በመጠለያው የተከሰተውን ሁኔታ ከሰሙ በኋላ እጅግ መደንገጣቸውን ነው ያስታወቁት፡፡
ኃላፊዋ ሁኔታው ቀጣዩን አስከፊ አደጋ አመላካች ነው ማለታቸውን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
ምላሽ ይስጡ