በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኘው አዲሱ አዳራሽ ውስጥ የሚያስፍልጉ መገልገያ ግበቶችን የማሟላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ትምህርት ቤቱ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የአሸናፊ ከበደ የአርት ሴንተር ዳይሬክተር አቶ ግርማ ይፍራሸዋ አዲሱን አዳራሽ ቦታውን የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ አንዳንድ ያልተሟሉ እቃዎች እንዳሉና የበጀት ችግር እንዳለባቸዉም አመላክተዋል።
አሁን ላይ ሁሉን ነገር ማሟላት ባይቻልም አስፍላጊ የሚባሉ መሰረተ ልማቶች ግን ሊሟሉ እንደሚገባ ገልጸዋል።
አዳራሹ በርካታ ዝግጅቶችን ማከናወን የሚያስችል ቢሆንም አንዳንድ አስፈላጊ እቃዎች ባለመሟላታቸው ምክንያት በተፈለገው መጠን እንዳይሰራበት አድርጓል ብለዋል።
እቃዎቹ ባልተሟሉበት መልኩ ዝግጅቶች ማድረግ የተቋሙን ስም ሊያበላሽ እና ተጠያቂ ሊያደርግ ስለሚችል እስኪሟላ በተወሰነ መልኩ ብቻ አንዳንድ ኹነቶችን ማድረጉ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት አዳራሽ አስፈላጊ ነገሮችን በማሟላት በርካታ ኪነ ጥበባዊ ኹነቶቸ እእዲሀገጁበት እና ለባለሙያዎችም እንዲጠቅም ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ