መብረቅ ከሚመታቸው ዛፎች መካከል አብዛኞቹ ይደርቃሉ፤ ነገር ግን ሳይንቲስቶች ከመብረቅ አደጋ የሚተርፉ ብቻ ሳይሆኑ በአደጋው ምክንያት የሚበቅሉ የዛፍ ዝርያዎች እንዳሉ አረጋግጠዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በአማዞን ባሉ አንዳንድ ግዛቶች ስለ አዳዲስ የዛፍ ዝርያዎች መረጃ ሲሰበስቡ መብረቅን የሚቋቋሙ ዛፎች እንዳሉ ፍንጭ እንዳገኙ ዘገባው ገልጿል።
እ.ኤ.አ. በ2015 በፓናማ ውስጥ የሥነ ምህዳር ጥናት ሲሰራ የነበረ አንድ ባለሙያ ይህንኑ ማረጋገጡ ተገልጿል፡፡ የሳይንስ ሊቃውንት ይህን ያልተለመደ እይታ ከመረመሩ በኋላ Dipteryx oleifera የተባለው ዝርያ የመብረቅ ጥቃቶችን በቀላሉ መቋቋም እንደሚችል መላምት አስቀምጠዋል፡፡ ከዚያ በኋላም የተደረገው ምርምር ይህንኑ አረጋግጣል ያለው የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ ነው፡፡
ጉዳዩን በሳይንሳዊ መንገድ ማረጋገጥ ከባድ ቢሆንም፤ መብረቅ በተደጋጋሚ የሚያጋጥምበት ቦታን በመለየት የጥናት ቡድኑ በመብረቅ የተመቱ የ93 ዛፎችን ውጤት በመከታተል ከሁለት እስከ ስድስት ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ ባደረጉት ጥናት አረጋግጠዋል።
ተመራማሪዎቹ ግኝታቸውን አስደናቂ ነበር ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ