ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ለአንድ ዓመት የስራ ዘመን በኃላፊነት እንደሚቆዩም ተገልጿል።
ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙ ይታወቃል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩን አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት በርዕሰ መስተዳድርነት ሲመሩ መቆየታቸውም የሚታወቅ ነው።
በትላንትናው ዕለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው አሰናብተዋቸዋል፡፡
አቶ ጌታቸው የተገኘው ሰላም እንዲጸና ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና አመራር የፌደራል መንግስት እውቅና እንደሚሰጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በዛሬው ዕለት እስከ ቀጣዩ ምርጫ ድረስ ለአንድ ዓመት ጊዜያው አስተዳደሩን በርዕሰ መስተዳድርነት እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል።
ምላሽ ይስጡ