መጋቢት 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት፤ ለጋዜጠኞች የሙያ ማረጋገጫ ለመስጠት እና የጋዜጠኞች ምዝገባ ለማከናወን ውይይት እና እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ፣ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞች እና የሙያ ማህበራት ጉዳዩን በተመለከተ የሕጋዊነት ጥያቄ እና ስጋቶቻቸውን ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤቱ ጋዜጠኞችን ወይም የሚዲያ ባለሙያዎችን የመመዝገብም ሆነ የሙያ ማረጋገጫ የመስጠት ተግባርና ኃላፊነት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1239/2013 አልተሰጠውም ብሏል ባለስልጣኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለዚህ የምክር ቤቱ ተግባር እውቅና የማይሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ