በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋም አካባቢ በመሆን አስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት መሰጠት ቆሟል እኛ እናሰራላችሁ በማለት ተቋሙ ለ5 ቀን 20 ሽህ የሚያስከፍለውን 28 ሽህ ብር በመቀበል የተሳሳተ መረጃ በመስጠትና ያልተገባ ክፍያ በመጠየቅ 24 የተቋሙን አገልግሎት ፈልገው የመጡ ደንበኞችን ያጭበረበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
ተቋሙ ከፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ በአደረገው ክትትል ግለሰቦችን ለህግ እንዳቀረባቸውና ተገልጋዮች የከፈሉትን ክፍያ ማስመለስ እንደቻለ ተናግሯል።
የኢሚግሬሽንን አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣ ደንበኛ በተቋሙ መረጃ ዴስክ በመቅረብ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚገባ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ