በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 400 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ።
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆን ከተመላሾች መካከል 33 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል ተብሏል።
በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3/ 2017 ዓ.ም እየተሰራ ባለው ስራ እስካሁን 12 ሺህ 317 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ምላሽ ይስጡ