የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲስተም ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ከኢንተርኔት አገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የድህረ ክፍያ አገልግሎቶች አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ገለጿል፡፡
ሲስተም ላይ ባጋጠም ብልሽት ምክንያት 905 እና 904 ነፃ የጥሪ ማዕከሎች እንዲሁም የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን ጨምሮ ከኢንተርኔት አገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የድህረ ክፍያ አገልግሎቶች፣ አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን አገልግሎቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ተመላክቷል፡፡
ደንበኞቹም ችግሩ ተፈትቶ የተቋረጠው አገልግሎት እስከሚመለስ ድረስ በአቅራቢያ በሚገኙ ዲስትሪክቶች ወይም አገልግሎት መስጫ ማዕከሎች በአካል ወይም በቀጥታ ስልክ በመደወል ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ