ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ሉዓላዊነቷን የሚገዳደሩ የውጭ ሀይሎች ሲገጥሟት እንደነበር ይታወቃል፡፡
ይህ አይነቱን ጣልቃ ገብነት ለማስወገድ የሀገር ሀብትን በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ፤ አሁንም ድረስ ወደ ኢትዮጵያ የሚያማትሩ ጣልቃ ገብ የውጭ ሀገራት በተለያዩ መንገዶች እጅ የመጠምዘዝ ሁኔታ እያሳዩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አንደንድ ያሏቸው አገራት በቴክኖሎጂ እና የመገናኛ ብዙሃን አማራጭ ጫና እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል፡፡ ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር በሚልም ጫና እያሳደሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ይህ አይነቱን ተጽዕኖ ለመቆጣጠር እና መፍትሄ ለማበጀት በመንግስት በኩል የተያዙ አቋሞች ስለመኖራቸው የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ አንዱ የመፍትኤ አማራጭ ሀገሪቱ ያላትን ሀብት በአግባቡ መጠቀም መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሀገሪቱን በቴክኖሎጂ በማበልጸግ ሉዓላዊነቷን ማስከበር ከተቻለ በየአቅጣጫው የሚገጥመውን የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነት መቀነስ እንደሚቻል አመልክተዋል፡፡
መንግስት የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመከላከል የሚሰራውን ስራ ዜጎች አንድነት እና ህብረትን በማጠናከር ማገዝ እንደሚገባቸው አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ