ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን 2.4 ሚለዮን ሜትሪክ ቶን ወይም 24,000,000( ሃያ-አራት ሚሊዮን) ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ገዝቶ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ከተያዘው እቅድ ውስጥ እሰከ መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 10 ሚሊዮን 741 ሺሕ 181 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በ20 መርከቦች ተጭኖ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን እና ከዚህም ውስጥ 9 ሚሊዮን 627 ሺህ 402 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን እንዲሁም 111,377.9 ሜ/ቶን ደግሞ በወደብ እንደሚገኝ ከማሪታይም ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በ20 መርከቦች ከተጫነው ውስጥ በ13 መርከቦች የተጫነው 737,968.1 ሜ/ቶን ዳፕ እንዲሁም በ7ቱ መርከቦች የተጫነው 336,150. ሜ/ቶን ዩሪያ የተሰኘው የአፈር ማዳበሪያ ሲሆን ወደ አገር ውስጥ ከተጓዘው ደግሞ 626,692.2 ሜ/ቶን (6,266,922 ኩንታል) ዳፕ እንዲሁም 336,048 ሜ/ቶን (3,360,480 ኩንታል) ደግሞ ዩሪያ የተሰኘው የአፈር ማዳበሪያ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በጠቅላላው ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው 962,740.2 ሜ/ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 808,145.2 ሚ/ቶኑ የተጓጓዘው በድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ሲሆን ቀሪው 154,595 ሜ/ቶኑ የተጓጓዘው በባቡር ነው ተብሏል፡፡
__
ምላሽ ይስጡ