በትራክ ውድድሮች ታሪክ ከፍተኛውን የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኘው የግራንድ ስላም ውድድር በጃማይካዋ ኪንግስተን ከተማ እየተከናወነ ይገኛል።
በቅርብ አመታት በውድድር ቁጥር ማነስ ምክንያት እየተቀዛቀዘ የነበረውን የትራክ ሩጫ ያነቃቃል ተብሎ የሚጠበቀው በቀድሞው የአራት ጊዜ የኦሊምፒክ አሸናፊ በማይክል ጆንሰን የተመሠረተው ይህ የትራክ ግራንድ ስላም ውድድር ዘንድሮ ሲከናወን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በአጠቃላይ 96 አትሌቶች የሚካፈሉበት አዲስ የትራክ ግራንድ ስላም ሊግ በአራት ግራንድ ስላም ውድድሮች የመጀመሪያ አመት እስከ 12.6 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጅቷል።
በሎስ አንጀለስ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው የግራንድ ስላም ትራክ ውድድር ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቬስትመንት ለውድድሩ ያደርጋል ።
ታዲያ በመጀመሪያው ዙር አትሌት ድሪቤ ወልተጂ በተሳተፈችበት 1500 ሜትር ውድድሩን በበላይነት አጠናቃለች። የገባችበት ሰአት ደግሞ 4:04:51 ነው።
ውጤቱን ተከተትሎ ያስመዘገችው ነጥብ ከእንግሊዛዊቷ ጋቢ ቶማስ ጋር እኩል 20 ነጥብ መሆኑን ተከትሎ የ100 ሺ የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ሽልማትን አንድላይ እንደሚጋሩ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ የግራንድ ስላም ትራክ ሻምፒዮና ዛሬ በሚደረጉ ወድድሮች ፍፃሜውን ያገኛል። በ4 ዘርፎች አሸናፊዎቹን ያሳውቃል። በ5000ሜትር ሴቶች ፆጌ ገ/ሰላማ እና እጅጋየሁ ታዬ እንዲሁም በ3000 ሜትር ሀጎስ ገ/ህይወት እና ጥላሁን ሀይሌ የሚሳተፉባቸው ውድድሮች ይጠበቃሉ።
ይህ ግራንድ ስላም ትራክ ውድድር በቀጣይ በማዬሚ ፤ ፊላደልፊያ እንዲሁም ሎስ ረንጀለስኝ ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ላይ ቀጥሎ እንደሚከናወን ለማወቅ ተችሏል።
በአንድ ሊግ የግራንድ ስላም የገንዘብ ሸልማቱ
1ኛ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር
2ኛ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር
3ኛ 30 ሺህ የአሜሪካ ዶላር
4ኛ 25 ሺህ የአሜሪካ ዶላር
5ኛ 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር
6ኛ 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር
7ኛ 12 ሺህ 500 የአሜሪካ ዶላር
8ኛ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መሆኑን የውድድሩ አዘጋጆች አሳውቀዋል።
ምላሽ ይስጡ