የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የአዋጁ መጽደቅ በህገ መንግስት የሚፈቀድና የፌደራል ስልጣን እና የክልል ስልጣን ተግባር በህገ መንግስቱ በአንቀጽ 51 እና 52 ላይ በግልጽ የተለዩ መሆኑን የህግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ተናግረዋል።
አዋጁ በህገ መንግስቱ ክልሎች ከአቅማቸው በላይ ሲሆን የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ የሚያደርጉበት ህግ የጣሰ አለመሆኑን፤ ክልሎች የተጣለባቸውን ሀላፊነት ባለመወጣታቸው እንደ ሀገር ያለው ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ መስፋፋቱን ተናግረዋል። በዚህም መልኩ የማሻሸያ አዋጁ ይሄን ለመፍታት የሚጠቅም መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ሌላኛው የህግ ባለሙያው አቶ መንግስቱ አበራ በበኩላቸው፤ የፌደራል መንግስቱ በክልሎች ጣልቃ እንዲገባ የሚያስችል አዋጅ መጽደቁ የፌድራልና የክልል መንግስታት የስልጣን ክፍፍል በጠበቀ መልኩ እና ለክልሎች የተሰጠው ስልጣን የማይጥስ ከሆነ የሚሰጠዉ ጥቅም ከፍ ያለ ነዉ ነገር ግን ስጋቶችን መቀነስ ይገባል ብለዋል፡፡
የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚያሻሽለው አዋጅ መጽደቁ በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልል ያለው ነባራዊ ሁኔታ ህግ የሚጥሱ ተግባራት ሊፈጸሙ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ምላሽ ይስጡ