አላግባብ የገዳ ባንክን ስም በመጠቀም ሰራተኞችን በባንኩ እናስቀጥራለን በሚል ገንዘብ ሲቀበሉ የነበሩ ህገወጦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገልጿል።
ከገዳ ባንክ ምስረታ አስቀድሞ ህገወጦች ሰራተኞችን በባንኩ ትቀጠራላቹ በማለት ገንዘብ ሲቀበሉ እንደነበረ በተደረገ የማጣራት ስራ መረጋገጡን ባንኩ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
ባንኩ ድርጊቱን አስመልክቶ ከማህበረሰቡ ጥቆማ እንደተሰጠውና ጉዳዩን ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ በመውሰድ ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን የባንኩ የህግ አማካሪ አቶ ሙለታ ድበል ተናግረዋል።
በባንኩ ስራ እቀጠራለሁ በሚል በርካታ ማህበረሰብ በህገወጦቹ ተታለው ከ35ሺ እስከ 100ሺ ብር ክፍያ መፈጸማቸውን የህግ አማካሪው ገልጸዋል።
ከወንጀለኞቹ ጋር ግንኙነት ያላቸው የባንኩ ሰራተኞችን በህግ ለማስጠየቅ የማጣራት ስራ መስራቱን በመግለጽ ማህበረሰቡ በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ካለው ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ስራ ፈላጊዎች በግለሰቦቹ ተታለው በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ክፍያ መፈጸማቸው የተገለጸ ሲሆን በአራቱም ወለጋ ዞኖች በኢሊባቦር፡ በሸገር ከተማ እና በሌሎችም አካባቢ ይገኛሉ ብለዋል።
ገዳ ባንክ ከተመሰረተ 2 ዓመቱ ሲሆን ባንኩ በግልጽ አሰራር ማስታወቂያ በማውጣት የስራ ቅጥር እየፈጸመ መሆኑን የገለጹት የባንኩ የህግ አማካሪ፤ ከዚህ አሰራር ውጪ በምንም አይነት መልኩ የስራ ቅጥር እንደማይፈጸም ማህበረሰቡ ተገንዝቦ ከህገ-ወጦች ድርጊት እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።
ምላሽ ይስጡ