👉ባለፉት ስምንት ወራት ከ7.72 ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች መከናወኑም ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሐብት 2.073 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተቋሙን የስምንት ወራት አፈጻጸም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል።
እስከ ፈረንጆቹ በፌብሩዋሪ 2025 መጨረሻ ድረስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 1.541 ትሪሊዮን፣ ጠቅላላ የብድርና የቦንድ ክምችት መጠን ብር 1.393 ትሪሊዮን፣ እንዲሁም አጠቃላይ ሐብት ብር 2.073 ትሪሊዩን መድረሱን በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
ባንኩ በዋና ዋና የአፈፃፀም መለኪያዎች የበጀት ዓመቱ ሲጀመር በኢንዱስትሪው የነበረውን የገበያ ድርሻ ማሳደግ መቻሉም በሪፖርቱ ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት 264 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር ብድር ባንኩ ለደንበኞች ማቅረቡንም አቶ አቤ ሳኖ ጠቅሰው፤ከዚህ ውስጥ 88 ነጥብ 2 በመቶው የተሰጠው ለግሉ ዘርፍ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
ባንኩ ብድርን ከማስፋፋት እና የዜጎችን የፋይናንስ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር አዳዲስ የብድር አይነቶችን እያስተዋወቀ እንደሚገኝም አመላክተዋል።
በዲጂታል አማራጭ717 ሺህ ደንበኞች የብድር አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ምላሽ ይስጡ