የአውሮፖ ህብረት በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህንና የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂነት ለማጎልበት 240 ሚሊዮን ዩሮ (32 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር) ድጋፍ አድርጓል።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፤ የአውሮፖ ህብረት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲመዘገብ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ህብረቱ ግብርና፤ ትምህርት፤ ለመሰረተ ልማት ግንባታ፤ የፋይናንስ ክፍተትን ለመሙላት የሚሰሩ ስራዎችን ያግዛል ብለዋል።
አውሮፖ ህብረትና የኢትዮጵያ ግንኙነት 50 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ገልጸው፤ ማክሮ ኢኮኖሚን ተግባሪዊ በማድረግ ኢኮኖሚዊ፤ ማህበራዊና የቴክኖሎጂ እድገትን እያሰመዘገበች ነው፤ የሀገርና የውጪ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እየስራች ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገርን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚን ተግባራዊ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እድገት እያሰመዘገበች ነው።
በስምምነት መሠረት የአውሮፓ ህብረት የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍን እንደሚሰጥ ጠቅሰው የኢትዮጵያን ልማት ለማሻሻል 240 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ኢንሼቲቪ ፕሮግራም በቀጠናው ሰላምን ለማረጋጋትና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ያመጣል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የድጋፉ የሽግግር ፍትህ፣ የፃታ እኩልነትን ለማጠናከር፤ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት፤መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን, የሕክምናና የስነ-ልቦና ማኅበራዊ ድጋፍ የአገልግሎት አቅርቦት ለማናጠናከር ይጠቅማል።
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የዲጂታል እውቀትንና ልምድን ለማሳደግ የሚውል ነው ሲሉም አክለዋል።
ምላሽ ይስጡ