ዘንድሮ ለ40ኛ ጊዜ በተከናወነው አመታዊው የማዬሚ ኦፕን ሜዳ ቴኒስ ውድድር በአሜሪካ ማዬሚ ግዛት ላይ ሲከናወን በሴቶች የአለም ቁጥር አንዷ አሪና ሳባሌንካ ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቃለች።
በሀርድ ሮክ ስቴዲየም በተከናወነው በዚህ ጨዋታ ላይ ቤላሩሲያዊቷ ሳባሌንካ አሜሪካዊቷን ጄሲካ ፔጉላን 7-5 እና 6-2 በድምሩ 2-0 በሆነ ውጤች ነው ማሸነፍ የቻለችው።
የ26 አመቱ የቴኒስ ተወዳዳሪ ሰርቦቿ እየከሸፉ ብዙ ጊዜ ሰሜታዊ እና ንዴት ውስጥ ስትገባ ይታይ ነበር። በዚ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ግን ሰርቦቿ ቢበላሹም ያለጥሩ ሰርብ ጨዋታውን ማሸነፍ እንደምችል ራሴን አሳምኜው ነበር በውጤቱም ደስ ብሎኛል ስትል ሀሳቧን ሰጥታለች።
የ3 ጊዜ የግራንድ ስላም ክብር ባለቤቷ አሪያና ሳባሌንካ ከዚ በፊት ባሳለፍነው ጥር ወር አውስትራሊያ ላይ በተደረገው የሜዳ ኦፕን እና ኢንዲያና ዌልስ ላይ ለፍፃሜ መብቃቷ አይዘነጋም።
በወንዶች የአለም ቁጥር 5ቱ አንጋፋው የ37 አመቱ ኖቫክ ጆኮቪች በቴኒስ ህይወቱ 100ኛ የዋንጫ ክብሩን ለማግኘት ከ19 አመቱ ወጣቱ ቼካዊ ተወዳዳሪ ያኩፕ ሜንሲክ ጋር ጋር ያደረገውን ጨዋታ በሽንፈት አጠናቋል።
ወጣቱ ያኩፕ ሜንሲክ ወደ ዚህ ስፖርት የተቀላቀልኩት ጆኮቪችን አይቼ ነው። አርአያዬ ነው ከሱ ጋር መጫወት ራሱ ለኔ ትልቅ ክብር ነው ሲል ለጆኮቪች ያለውን አክብሮት አሳይቷል።
ጆኮቪች ከጂሚ ኮነርስ እና ሮጀር ፌዴረር በመቀጠል 100 ክብሮችን ማሳካት የቻለ 3ኛው የቴኒስ ተወዳዳሪ መሆን የሚችልበትን እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ከዛ ጎን ለጎን የ24 ጊዜ የግራንድ ስላም ክብር ባለቤቱ ሰርቢያዊው ጆኮቪች ይህንን የማዬሚ ሜዳ ኦፕን የቴኒስ ውድድር ለ7ኛ ጊዜ ማሸነፍ የሚችልበትንም እድል አምክኗል።
የማዬሚ ሜዳ ኦፕን ቴኒስ አሸናፊዎቹ 1 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት እንዲሁም በአለም የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ 1000 ነጥቦች የሚያስገኝ በአይነቱ ትልቅ ይዘት ያለው የውድድር መድረክ እንደሆነ ይታወቃል።
በሚካኤል ደጀኔ
ምላሽ ይስጡ