የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን በውክልና በተሰጣቸው የተሽከርካሪ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ፈቃድ ላይ የጎላ ክፍተት በፈጸሙ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
በተሽከርካሪ ዓመታዊ ቴክኒክ ችግር ምክንያት የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎችን ለማስቀረት ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ለሚያካሄዱ ተቋማት ውክልና ሰጥቶ በማሰራት ላይ እንደሚገኝ ያስታወቀው ባለስልጣኑ፤ የተቋማቱን የስራ እንቅስቃሴና አፈጻጸም በመመዘንና በመገምገም የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ከባለስላጣኑ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሰሞኑን የጎላ ክፍተት በተገኘባቸው 24 ተቋማት ላይ የተለያዩ የዲሲፕሊን እርምጃዎችን መውሰዱን አስታውቆ፤ የጎላ ጉድለት በታየባቸው 2 የምርመራ ተቋማት ፈቃድ የመሰረዝ እርምጃ መውሰዱንና 4 ተቋማት ደግሞ ለሶስት ወራት ታግደው ክፍተታቸውን እስኪያርሙ የመዝጋት እርምጃ እንደተወሰደባቸው አስታውቋል፡፡
6 ተቋማት ለአንድ ወር ታግደው ክፍተታቸውን እስኪያርሙ ስራ እንዲያቆሙ የተደረገ ሲሆን፣ 12 ተቋማት ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንና በአሰራራቸው የተሰተዋሉትን ጉድለቶች በአንድ ወር ውስጥ በአስቸኳይ እንዲያርሙም ውሳኔ መተላለፉ ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ