ባለፉት 15 ቀናት ምንም አይነት ነዳጅ ወደ ክልሉ አለመግባቱን ያስታወቀው የትግራይ ክልል የንግድና ሸማቾች ጥበቃ ቢሮ፣ በመቀሌ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ከ15 ሺህ በላይ ሊትር ነዳጅ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር መዋሉን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል፡፡
ባለፉት 15 ቀናት ወደ ክልሉ ምንም አይነት ነዳጅ ባለመግባቱ በመቀሌ ከተማ 17ሺህ ሊትር ገደማ ነዳጅ በህገወጥ መንገድ ለሽያጭ ሲዘዋወር መያዙን በክልሉ የንግድና ሸማቾች ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ክንደያ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ ግን በቀን ከአንድ እስከ ሁለት ተሽከርካሪ ነዳጅ እየገባ መሆኑን የሚገልጹት ዳይሬክተሩ በክልሉ 64 ማደያዎች እንዳሉ አስታውቀዋል።
አቅርቦቱ ካለው ፍላጎት አንፃር የማይመጣጠን በመሆኑ ተጨማሪ መጠን እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡
ስለተፈጠረው የአቅርቦት እጥረት ምክንያት መረጃ እንደሌላቸውና በጉዳዩ ዙሪያ ለመነጋገር እንዲሁም ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት በክልሉ በቀን ከ500 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ይገባ እንደነበር የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ የአቅርቦቱ መቆራረጥ በትራንስፖርት፤ በእህልና በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንዲስተዋል አድርጓል ብለዋል።
ምላሽ ይስጡ