ለአጭር ጊዜ የዘገባ እና የቀረፃ ስራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚመጡ የውጪ ሀገር መገናኛ ብዙኃን እና የፊልም ድርጅቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል፡፡ ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ በታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች እንዲሁም ባህላዊ እሴቶች ዙሪያ ዘጋቢ ፊልም ለመስራት፣ ከመንግስት ኃላፊዎችና ከታዋቂ አትሌቶች ጋር ቃለ-መጠይቅ ለማድረግ፣ እንዲሁም ለሀገር አቅፍ እና አለም አቀፍ ስበሰባዎች የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ፈቃድ ለጠየቁ ለ353 የውጪ ሀገር መገናኛ ብዙኃንና የፊልም ድርጅቶች ፈቃድ መስጠቱን ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታዉቋል፡፡
ለቁጥሩ መጨመር የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ እና የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ጨምሮ በርካታ አህጉራዊ እና አለምአቀፍ ስበሰባዎች እና ኹነቶች መካሄዳቸው እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች መስፋፋታቸው ጥሩ አጋጣሚ መፍጠሩን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የመገናኛ ብዙሃን ፍቃድ ምዝገባና ዕውቅና ዴስክ ኃላፊ አቶ ደሴ ከፍአለ ተናግረዋል፡፡
አክዉም በቅርቡ የተሰሩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች የበርካታ ውጪ ሀገር መገናኛ ብዙኃን እና የፊልም ድርጅቶችን ቀልብ እየሳቡ እንደሆነ ፤በዚህም የሀገራችንን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች፣ ባህላዊ እሴቶች፣ እንዲሁም ወቅታዊ ኹነቶችን ለውጪው ዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ እድል መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡
የተለያዩ ኹነቶች በመዲናዋ አዲስ አበባ መከናወኑ የዉጭ ሚዲያዎች የሀገባ ተደራሽነት እንዲጨምር አድርጎታል ብለዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ