አለም አቀፍ የሜትሮሎጂ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ64ተኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ44ተኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት ተከብሮ መዋሉ ተገልጻል፡፡ በአለም ሀገራት ከአየር ንብረት ለዉጥ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መምጣታቸዉ ይገለጻል፡፡
የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል፤ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ትንበያ ስርዓት ለመዘርጋት የሜትሮሎጂ መረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎችን የማስፋፋት ስራ ትኩረት በመስጠት ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት የሜትሮሎጂ መሰብሰቢያ አማራጮች በማዘመን እና በማስፋፋት የአየር ሁኔታን ዘመኑ ባፈራቸው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች በመጠቀም ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ለመማድረግ ኢንስቲትዩቱን በሰዉ ሃይልና በመሳሪያ የማደራጀት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአየር ሁኔታን ዘመኑ ባፈራቸው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች በመጠቀም ፤ መረጃዎችንም በባለሙያ በማስተንተን ለግብርና፣ ለውሃ ፣ለጤና እና ለቅድመ አደጋ ስጋት ጥቆማና ችግሮችን መቀነስ በሚያስችሉ ጥቆማዎች ዙሪያ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የሚኖረዉን ግንኙነት በማጠናከር ፤ለምላሽ ሰጪ አካላት ምክረ ሀሳብ የሚሰጥበት መድረክ በቀጣይ ቀናት እንደሚዘጋጅም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
ምላሽ ይስጡ