የአለማችን ትልቁ የፍልሚያ መድረክ የሆነው እና የሚክስድ ማርሻል አርት ክህሎት ያላቸው ተፋላሚዎች በየክብደት እርከናቸው ተከፋፍለው በሚያከናውኑት የፍልሚያ መድረክ ትላንት በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ግዙፉ 02 አዳራሽ ላይ የሚከናወን ይሆናል።
ታዲያ በምሽቱ ተጠባቂ የነበረው የእንግሊዛዊው የቀድሞ መለስተኛ ከባድ ሚዛን ወይም Welterweight የቀበቶ ባለቤት የሆነው ሊዮን ኤድዋርድስ እና ከአሜሪካዊው ሻን ብሬዲ ጋር ያደረጉት ፍልሚያ ሲሆን ሻን ብሬዲ ማንም ባልጠበቀው መልኩ ኤድዋርድስን 4ኛው ዙር ላይ በበቃኝ አሳምኖ በመርታት ጣፋጭ ድል ተጎናፆፏል።
አሜሪካዋው ብሬዲ የመጀመሪያ ሴት ልጁን ከማግኘቱ እና ፍልሚያውን በአጭር ጊዜ ተቀብሎ የተጋጣሚው ኤድዋርድስ ሀገር ወደሆነችው እንግሊዝ አቅንቶ 4ቱንም ዙር የበላይነቱን በመውሰድ ማሸነፍ ችሏል።
ፕሮፌሽናል የMMa ሪከርዱ 17 ጊዜ ሲያሸንፍ 1 ሽንፈት ብቻ ያጋጠመው ብሬዲ ከ2022 በኋላ 3ኛ ተከታታይ ድሉን መጎናፀፍም ችሏል።
የቀድሞ ሻምፒዮን ሊዮን ኤዱዋርድስ በ2024 ሰኔ ወር ላይ ቀበቶውን በቤላል ሙሀመድ ከተነጠቀ በኋላ ያደረገውን ሁለተኛ ፍልሚያ ማሸነፍ አልቻለም። ሀገሩ ላይ በተደረገው ይህ ፍልሚያ ላይ ባሳየው ደካማ እንቅስቃሴ በራሱ ማዘኑን እና ጠንክሮ እንደሚመለስ አሳውቋል።
በዚህ ፍልሚያ የፌነርባቼው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆን ጨምሮ የቶተንሀም እና ቼልሲ እግርኳስ ተጫዋቾች የሆኑት ሪቻርልሰን እና ዌስሊ ፎፋና በቦታው በመገኘት ፍልሚያውን ከተመለከቱ የስፖርቱ ቤተሰቦች መካከል ስማቸው ይጠቀሳል።
በሚካኤል ደጀኔ
ምላሽ ይስጡ