እንደ ሀገር ህብረተሰቡ እንዲሁም ስፖርቱን ከመንግስት በተጨማሪ ይደግፋሉ ተብለዉ የሚታሰቡ ባለሀብቶች ስለ ቴኳንዶ ስፖርት ግንዛቤው ስለሌላቸው ተደጋጋሚ የበጀት እጥረት እንዲገጥመው ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ ፍቅሩ ተቋም፤ የቴኳንዶ ውድድሮች በተለያዩ የአለም ሀገራት የሚካሄዱ ቢሆንም እንደ ሀገር ካለው የበጀት ችግር አኳያ ብዙዎቹ ላይ ተሳታፊ መሆን አልተቻለም ብለዋል፡፡
በመጪው ሚያዝያ ወር አለም አቀፍ የቴኳንዶ ውድድር ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በመግለፅ ይህ ውድድር ኢትዮጵያ በሌሎች ሀገራት በሚዘጋጁ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ እንድትሆን እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡ በበጀቱ እና ትኩረት ባለማግኘቱ ሳቢያ የተሻለ ውጤት ማግኘት እንዳልተቻለ የገለፁ ሲሆን ከመንግስት ባሻገር ማህበረሰቡ ውስን ስፖርቶች ላይ ትኩረት ማድረጉ በሚፈለገው ልክ አንዳንድ ስፖርቶች እንዳያድጉ ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
መንግስት ለዘርፉ የተወሰነ በጀት ቢመድብም የሚደረገው እገዛ ውስን በመሆኑ ተሳታፊዎች የተሻለ አንዳይሰሩ እና በአለም አቀፍ ደረጃም ተወዳዳሪ መሆን እንዳይችሉ አደርጓል ብለዋል፡፡
የሚመከታቸው አካላት የቴኳንዶ ስፖርትን እንዲታወቅና ያለበት የበጀት ችግር እንዲፈታ ማድረግ ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ