መጋቢት 13 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በየአመቱ የማጓጓዝ አቅሙን እያሳደገ የመጣው የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አ.ማ ሃምሳ በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያን የወጪ ገቢ ጭነት ለመሸፈን አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ባቡሩ ካርጎ የማጓጓዝ አቅሙን በየአመቱ በ14 ነጥብ 2 በመቶ እያሳደገ መምጣቱን ገልጾ፤ ወደ ውጭ ከተላከው ቡና 98 በመቶ የሚሆነው በባቡር የተጓጓዘ ሲሆን ማዳበሪያን ጨምሮ የመልቲ ሞዳልና ዩኒ ሞዳል ኮንቲነር ጭነቶችን፣ የቁም እንስሳትን፣ ከባድ ማሽኖችን፣ አውቶቡሶችና አዳዲስ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ያጓጉዛል ነው የተባለው፡፡
የሚበላሹ ጭነቶችን በኮንቴነርር አሽጎ በማጓጓዝ ጥራታቸውን እንደጠበቁ ለውጪ ገበያ በማቅረብ ከውጭ ንግዱ ሊገኝ የሚታሰበውን ገቢ በማስጠበቅ በኩል ሚናውን እየተወጣም ይገኛል ነው የተባለው፡፡
የኢት-ጅቡቲ ባቡር አ.ማ የኢትዮጵያን ወጪ ገቢ ጭነት ሃምሳ በመቶ የሚሆነውን ለመሸፈን፣ በየቀኑ 14 ባቡሮችን በማሰማራት አገልግሎት መስጠት፣ የጭነት ባቡር ጉዞ ፍጥነትን በሰዓት ወደ 58 ኪሎ ሜትር ለማድረስ እንዲሁም በባቡር የሚሰጠውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ዲጂታሊዝ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ