መጋቢት 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ በሪሙጋ ቀበሌ በአሰቃቂ ሁኔታ የግድያ ወንጀል በፈፀመ ወንጀለኛ ላይ የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተወሰነ።
ተከሳሽ መሀመድ አክመል በቀቤና ልዩ ወረዳ በሪሙጋ ቀበሌ በልዩ ስሙ በተለምዶ ጎጥ 6 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መስከረም 15/01/2017 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 4:30 አካባቢ የግል ተበዳ አቶ ሸሪፍ ኑሮን በያዘው ክላሺንኮቭ መሣሪያ የግራ እግሩን ተኩሶ በመምታትና ከጉልበት በታች አካሉን በመጠረቢያ በመቁረጥ ባደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት የግል ተበዳይ ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ እንዲሁም የሟችን አንድ እግር ሌላ ቦታ ወስዶ በመደበቅ እንዲሁም የተለያዩ የሠውነት ክፍሎቹን በመቆራጥ አሰቃቂ ወንጀል ፈፅሟል።
ከሳሽ የቀቤና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ አቃቢ ህግ በተከሳሽ መሀመድ አክመል ላይ የወንጀል ቁጥር 539 (1) (ሀ) ተላልፋል በሚል በአቃቤ ህግ ክስ ቀርቦበታል፡፡
ተከሳሹ ክሱ ተነቦለት እምነት ክህደት ቃሉ ሲጠየቅ ክሱን አልቃወምም ድርጊቱንም አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አደለሁም በማለት ክዶ በመከራከሩ ፍርድ ቤቱም ለአቃቤ ህግ በክሱ ላይ የጠቀሳቸው የሠው እና የሠነድ ማስረጃዎች አቅርቦ እንዲያሰማ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ዐ/ህግም አሉኝ ያላቸዉን የሠውና የሠነድ ማስረጃ አቅርቦ የተሠሙ ሲሆን ማስረጃዎቹም ተመርምረው ተከሳሹ በበቀረበበት የግድያ ወንጀል ተመስክሮበታል ነው የተባለው፡፡
አቃቤ ህግ በቃረበው የሠውና የሠነድ ማስረጃ መሠረት በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 149 መሠረት ጥፈተኝነት ፍርድ ተሠጥቶት ጥፋተኛ በተባለበት የህግ አንቀፅና በተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሠረት በመጋቢት 08/2017 ዓ.ም ጥፋተኛ በተባለበት አንቀፅ መሠረት በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።
ቃጣቱንም የወልቂጤ ማረሚያ ቤት ተከታሎ እንዲያስፈፅም ትዛዝ እንደተሰጠው ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ