መጋቢት 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዳኛው ትዕዛዝ በትራምፕ አስተዳደር እርምጃ ሁሉም የUSAID ሠራተኞች በአስተዳደር ፈቃድ ላይ ያሉትን ጨምሮ ኢሜይልም ሆነ የሥራ ኮምፕዩተራቸውን ዳግም መጠቀም እንዲችሉ ይጠይቃል።
ሆኖም ግን ከሥራ መባረርን ስለመከላከሉም ሆነ ድርጅቱን ዳግም ለማቋቋም ስለማስቻሉ የተባለ ነገር የለም።
ፌደራል ዳኛው የUSAIDን እንቅስቃሴ በመገምገም መረጃዎችን በማጋለጥ ላይ የሚገኘው በቢሊየነሩ ኤለን መስክ የሚመራው የመንግሥት አስተዳደር ስኬታማነት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ DOGE የተሰኘው ዘርፍ በድርጅቱ ላይ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዳይወስድ ማገዳቸውም ዘርፉ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት ሳይጥስ እንዳልቀረ ማመላከቱን ዘገባዎች ጠቅሰዋል።
በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተሾሙት ኤለን መስክ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በሚጽፉትም ሆነ በይፋ በሚሰጡት መግለጫ DOGEን ሙሉ ለሙሉ እንደሚቆጣጠሩት እየጠቆሙ ነው።
ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት የUSAID ሠራተኞች እና ኮንትራክተሮች መስክ እና የሚመሩት ዘርፍ ሕገ መንግሥቱን የጣሰ እርምጃ እየወሰዱ ነው ሲሉ ከሰዋል።
መስክ ደጋግመው USAIDን እንዳያንሰራራ አድርገው እንዳንኮታኮቱት መግለጻቸውን ዳኛው አመልክተዋል።
ጠበቆቻቸው ግን ዳኛው የሰጡት ውሳኔ ድርጅቱን ለማፍረስ የተወሰዱ አብዛኞቹን እርምጃዎች በውጤታማነት ያስቆማል ወይም ይለውጣል የሚል እምነት አላቸው።
የUSAID ሥራ መቆሙን ተከትሎም በተለያዩ ሃገራት የመድኃኒት አቅርቦት ችግር መከሰቱ እየተነገረ ነው።
ኬንያ ውስጥ ኤች አይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ከወዲሁ በመድኃኒት እጦት ሕይወታቸው ለአደጋ ሊጋለጥ እንደሚችል ስጋት እንደገባቸው መግለጽ መጀመራቸውን የዘገበው ዶይቼ ቬለ ነው፡፡
ምላሽ ይስጡ