የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና ክትትል ሊያገኝ መቻሉን አስታውቋል፡፡
ሪጅኑ በ196 ሺሕ ደንበኞች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ክትትል 13 በስማርት ቆጣሪዎች፣ 69 በቅድመ ነጠላና ባለሦስት ፌዝ ቆጣሪዎች እና በ29 የድህረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ላይ ስርቆቱ መፈጸሙን ገልጿል፡፡
ዘመናዊ ቆጣሪዎች (ስማርት ) ላይ የተደረገው ስርቆት የታወቀው ቆጣሪዎቹ ወደ መረጃ ቋት በሚልኩት መረጃ መሆኑን የሸገር ሪጅን ኢነርጂ ማኔጅመንት ማናጀር አቶ ግርማ ወግበላ አስታውቀዋል፡፡
ማናጀሩ የኃይል ስርቆት በፈፀሙ ደንበኞች ላይ ከ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ እንዲከፍሉ በማድረግ ሊባክን የነበረ ከ17 ሚሊየን በላይ ኪዋት ሰዓት ከብክነት ታድገናል ሲሉ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም የኃይል ስርቆት ሲፈጽሙ በተገኙ ደንበኞች ላይ ክስ የተመሰረተ መሆኑን አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡
የኃይል ስርቆት መፈፀም በወንጀል የሚያስከስ ሲሆን እስከ አምስት ዓመት ድረስ በእስራት እንዲሁም እስከ 20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት የሚያስቀጣ ነው፡፡
ምላሽ ይስጡ