ለሚዲያ ባለሙያዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ ዓለም ዓቀፍ የሙያ ምስክርነትን የሚያረጋግጥ አንድ ወጥ መታወቂያ ሊዘጋጅ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ምዝገባ ፣ የሙያ ማረጋገጫ እና በብሔራዊ ሚዲያ ሽልማት እውቅና ዙሪያ ያተኮረ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ አካሂዷል።
አውደ ጥናቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኝነት ስራ በታማኝነት፣ በብቃት እና በተጠያቂነት እንዲተገበር ለማስቻል የሚዲያ ባለሙያዎችን ሙያዊ እውቅናን በመስጠት ህጋዊ ለማድረግ ግልፅ የሆኑ መስፈርቶችን በማስቀመጥ ሁለተናዊ ማእቀፍ ለመዘርጋት አላማ ያደረገ መሆኑን ምክር ቤቱ ማስታወቁን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ ዓለም ዓቀፍ የሙያ ምስክርነትን የሚያረጋግጥ ዲጂታል ስርአቱን የተከተለ የዲጂታል መታወቂያ በሃገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ መታወቂያ ለሚዲያ ባለሞያዎች እንደሚዘጋጅ መናገራቸው ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ