በትግራይ ክልል አዲስ መጤ ‹የዛፍ አንበጣ› የተባለ ተምች መከሰቱን እና እስከአሁንም በ1 ሺህ 800 ሄክትር መሬት ላይ እንደተሰራጨ በግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ በላይነህ ንጉሴ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
የዛፍ አንበጣው መነሻው ኤርትራ እንደሆነ የሚገልጹት መሪ ስራ አስፈጻሚው፣ አሁን ላይ በዋናነት የሚያጠቃው ቋሚ ሰብሎችን፤ የእንስሳቱን የግጦሽ ሳር እና አንዳንድ የዛፍ አይነቶችን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የአንበጣው ባህሪ እንደ ሌላው የአንበጣ ዝርያ በስፋት ተንቀሳቃሽ እንዳልሆነና በአንድ ዛፍ ላይ ወይም በአንድ አካባቢ ብዙ ጊዜ የመቆየት እድል እንዳለው የሚገልጹት አቶ በላይነህ፣ በተደረገ የርብርብ ስራ 50 በመቶ የሚሆነውን መቆጣጠር እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡
ግብርና ሚኒስቴር አንበጣው በተከሰተበት አካባቢ የከፍ ጉዳት እንዳያደርስና ወደ ሌሎችም ክልሎች እንዳይዛመት ከክልሉ ግብርና ቢሮና ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴሩ አዲሱን የዛፍ አንበጣ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋትና ወደ ሌሎች አጎራባች ክልሎች እንዳይዛመት ለማድረግ ከክልሉ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ ነው ኃላፊው ያስታወቁት፡፡
ምላሽ ይስጡ