የድብልድ ማርሻል አርት ክህሎት ያላቸው ተፋላሚዎች በየክብደት እርከናቸው ተከፋፍለው የሚያከናውኑት የፍልሚያ አለም በተለምዶ Professional fighters league ወይም PFl የፍልሚያ ጨዋታዎች በቀጣዩ የፈረንጆቹ ወር እንደሚከናወን ተቋሙ አሳውቋል።
የፈረንጆቹ አዲስ አመት 2025 ከገባ በኋላ የሚከናወን የመጀመሪያው ፍልሚዪ ሲሆን በአሜሪካ ፍሎሪካ ግዛት በUniversal studio የሚከናወን ይሆናል። በ20 የተለያዩ ቁልፍ የሚድያ ማሰራጫ ጣብያዎች ፍልሚያዎቹን ስረሰጭት የሚሸፍኑ ሲሆን በ190 ሀገራት ላይ የሚተላለፍ ይሆናል።
በዚ የፍልሚያ ውድድር ምዕራፍ ላይ በወንዶች ከቀላል ሚዛን አንስቶ እስከ ከባድ ሚዛን ድረስ እንዲሁም በሴቶች በቀላል ሚዛን ብቻ ተፋሊሚዎች በየ ክብደት እርከኑ ለ500 ሺ ዶላር ከፍተኛ ትንቅንቅ ያደርጋሉ። ተቋሙ PFL በአጠቃላይ ለነዚህ ፍልሚያዎች በድምሩ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ሽልማት ስለማዘጋጀታቸው ለማወቅ ተችሏል።
የድብልቅ ማርሻል አርት እንዲስፋፋ ለማድረግ የራሱን ትልቅ ሚና እየተወጣ የሚገኘው ይህ ተቋም በአለም አቀፍ ደረጃ ከ650 ሚሊዮን በላይ ተከታታዮች ያሉት ተቋም ነው።
በሚካኤል ደጀኔ

ምላሽ ይስጡ