ፊልም ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ ተሰጥዖን የሚጠይቅ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ያንን ገጸባህሪ ወክለዉ የሚጫወቱባቸዉ የተለያዩ አይነት ዘርፎች በትክክል መላበስ እንደሚያስፈልግም ይታመናል፡፡ በዚህም በዘርፉ በርካታ ተዋንያን በስፋት የሚሳተፉበት ቢሆንም ገፀ ባህሪያትን ተላብስዉ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ክፍተቶች እንደሚታዩባቸው ትችት ሲቀርብበት ይስተዋላል፡፡
ለአብነትም የህክምና ባለሙያ፤ በህግ እና ፍትህ ዙሪያ ፤ዉትድርና እና ሌሎችም ዘርፎች የራሳቸዉ የሆነ ጥልቅ ግንዛቤን የሚጠይቁ ናቸዉ፤ሆኖም ባለሙያዎች የተሰጣቸዉን ድርሰት ተላብሶ ከመጫወት የዘለለ እዚህ ዘርፍ ላይ ማወቅ ያሉብኝ ነገሮች ምንድናቸዉ የሚለዉን ሲተገብሩት አይስተዋልም፡፡
የፊልም ደራሲና አዘጋጅ ሀብታሙ ሚደቅሳ እንደሚገልፀው ፊልም ሲሰራ እራሱን የቻለ አካሄድ እንዳለው በመግለጽ ደራሲውና አዘጋጁ ከጸሁፉ ባለፈ ሙያዊ ግንዛቤ ስለማይኖረው የግድ በዘርፉ የተሰማራውን ባለሙያ በማናገር ያን ሙያ ተላብሶ የሚተውነውን ተዋናይ ሙያዊ እገዛ እንዲያገኝ ይደረጋል በሏል፡፡
ከላይ የተነሳውን ሀሳብ የሚያጠናክረው በአላቲኖስ ፊልም ማህበር የፕሮግራም አዘጋጅ እና የካሜራ ባለሙያ ሱራፌል አንዳርጌ ፊልም ትልቅ ጥበብና ትውልድ የሚያየው በመሆኑ ጥልቅ ጥናት ይፈልጋል በማለት ይገልጻል፡፡
የፊልሙ ደራሲና አዘጋጅ ሙያን የተመለከተ ገጸ-ባህሪ በድርሰቱ ሲያካትት በቅድሚያ ለሚመለከተው ባለሙያ ጽሁፉን በመላክ ማስገምገምና እርምት ሊወስድ ይገባል ብሏል፡፡
የፊልም ኢንደስትሪ በኢትዮጵያ በእድገት ላይ ካሉ ዘርፎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ምላሽ ይስጡ