በሃገሪቱ በኩላሊት በሽታ የተጠቁ ህፃናት ዲያሊስስ የሚያደርጉበት የህክምና መስጫ ተቋም አለመኖሩን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ህክምና የኩላሊት ስፔሻሊስ ዶክተር ሀንድሰም ዲክሲሳ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ህፃናት እንደ አዋቂ ሁሉ በኩላሊት በሽታ እንደሚጠቁ የገለፁት ዶክተር ሀንድሰም በህፃናት ላይ በአብዛኛው በሽታው ሚከሰተው ሲወለዱ ጀምሮ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
ከ1 ሚሊየን ህጻናት 75 የሚሆኑ በበሽታው የተጠቁ መሆናቸውን ጥናቶች እንደሚያሳዩ ያስታወቁ ሲሆን፤ዲያሊስስ የሚፈልጉት ህፃናትም ከፍተኛ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
እንደ ሀገር ህፃናት ዲያሊሲስ የሚያደርጉበት ድንገተኛ የህክምና ማዕከል አለመኖሩ ለህፃናት የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆኑን ያሳየ ነው ያሉት ስፔሻሊስቱ፤ በቀጣይ ህፃናት ዲያሊሲስ የሚያደርጉበትም ሆነ ንቅለ ተከላ የሚደረግበት ምቹ ማዕከል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በህፃናት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያመጡ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት በጤና ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የአዕምሮ ጤና ዴስክ ሀላፊ ዶክተር ሰላማዊት አየለ ናቸው፡፡
እንደ ሀገር ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ትኩረት የተሰጠው ለአዋቂ መሆኑን እና ህፃናት ከአዋቂው ጋር አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚደረግበት ሁኔታ መኖሩን አብራርተዋል፡፡
ይህ የሆነው ደግሞ እንደ ሀገር ያለን የኢኮኖሚ ውስንነት ነው ያሉት ሀላፊዋ በቀጣይ አገልግሎቱን ለማስፋት ከሚመከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የህፃናት ኩላሊት ህክምና ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከ6 እንደማይበልጡ ተገልጿል፡፡
ምላሽ ይስጡ