መንግስት የፈጠራ ባህልን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የኢትዮ ሮቦ- ሮቦቲክስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በበኩላቸው አሁንም መንግስት ለዘርፉ ከዚህ በላይ ትኩረት በመስጠት መስራትና ማስፋፋት እንደሚገባው አመላክተዋል፡፡
መንግስት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የሮቦ ሮቦቲክስ ወድድሮችን በማዘጋጀትና ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር እንዲከተሉ በማድረግ ዘርፉን እያስፋፋ መሆን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ማስፋፋት ባለሙያ አቶ የኔዓለም ዲባ ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን ወክለው በቻይና በተደረገው የሮቦቲክስ ወድድር ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች ከ27 ሀገራት 3 ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን በማስታወስ መንግስት የፈጠራ ባህልን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮ ሮቦ- ሮቦቲክስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሰናክሬም መኮንን በበኩላቸው ተቋማቸው በሮቦቲክስ ዘርፍ በግል ማስተማር የጀመረ የመጀመሪው ተቋም መሆኑን ገልጸው፤ ዓለም እ.ኤ.አ በ2050 ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝድ እንደምትሆን ትንበያዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
በርካታ ሀገራትም ቴክኖሎጂን በማስፋፋት ረገድ ብዙ ስራ እየሰሩ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያም የተጀመሩ ስራዎች እጅግ የሚበረታቱ ቢሆኑም ይህንኑ በማስፋፋት በመላው ሀገሪቷ በትምህርት ስርዓት እንዲሰጥ መሰረታዊ ግብዓቶችን ማሟላት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ከትላንት መጋቢት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በዲዛይን፤ በኢንጂሪንግና በፕሮግራሚንግ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎች በአሜሪካን ሀገር በሚደረገው ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡
ምላሽ ይስጡ