በተለያዩ ተቋማት እንዲሁም በተለያየ መስክ ላይ የሚገኙና በልምድ የሚሰሩ ዜጎች ያላቸው ምርታማነት አንሳ በመሆኑ በተለያዩ ዘርፎች የሚፈለገውን ያህል ውጤት አለመገኘቱን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል።
ከ3.5 ሚሊየን በላይ ዜጎች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ እንደሚገኙና በተቋማቱ የዜጎችን ክህሎት ለማብቃት በተለያዩ መስኮች መደበኛ እንዲሁም አጫጭር ስልጠናዎች እንደሚሰጥ የገለጹት የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በተቋማት በኩል ስልጠና ያላገኙና በተለያየ መስክ በስራ ላይ የተሰማሩ ዜጎችን ምርታማነት ማሳደግ እንዲቻል prior of learning በሚል ስልጠናዎችን በመስጠት ክህሎታቸውን እና እውቀታቸውን የማሳደግ እና እውቅና የመስጠት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም በርካታ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ እንዲቻል እንዲሁም የዜጎችን ስራ የማግኘት ፍላጎት መሰረት በማድረግ አጫጭር ስልጠናዎችን በስፋት የመስጠት ብሎም ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማድረግ እየተሰራ እንዳለም ነው የገለጹት።
ገበያው ላይ የሚፈለጉ እና የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎችን ማጠናከር እንደሚገባ የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው በበርካታ ኢንዱስትሪዎች የሚስተዋለውን የክህሎት ችግር ለመቅረፍ በስራ ላይ ያሉ ዜጎችን ማሰልጠንና የክህሎት ልምዳቸው እንዲሻሻል ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
ምላሽ ይስጡ