የፌዴራል መንግስት፣ የአለም ጤና ድርጅት /WHO/ን ጨምሮ በውጪ ሃገራት ያሉ የትግራይ ተወላጆች የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የበጀትና የቁሳቁስ ድጋፎችን እያደረጉ እንዳሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል፡፡
ይሁን እንጅ በጦርነቱ የወደሙት ትምህርት ቤቶች ቁጥራቸው በርካታ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ጠግኖ ማጠናቀቅ እንዳልተቻለ ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለፁት የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራር አቶ ጣዕመ አረዶም ናቸው።
መሰረተ ልማቶቹን ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት ተደርጎ የተወሰኑት ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ቢደረግም፤ በተለይ በክልሉ ገጠራማ አካባቢ የመሰረተ ልማቱ ባለመጠገኑና የመጠለያ ካንፕ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ባለመለቀቃቸው ተማሪዎች በዛፍ ጥላ ስር እንዲማሩ አስገድዷል ብለዋል፡፡
በመሆኑም አሁን ላይ በክልሉ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸውን ነው ያስታወቁት።
ከጦርነቱ በኋላ በስደትና መፈናቀል ምክንያት ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ በርካቶች መሆናቸውን የሚገልፁት አቶ ጣዕመ፤ የምግብና የገንዘብ አቅም የሌላቸውም ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንደማይልኩ አስታውቀዋል፡፡
ተማሪዎቹን እና የትምህርት ተቋማቱን ለመደገፍ ሁሉም አካላት አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ምላሽ ይስጡ