የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ከዩክሬን አቻቸው ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በቤተ-መንግስት ያልተግባቡበትን ንግግር ካደረጉ በኋላ ለዩክሬን የሚሰጠውን ወታደራዊ እርዳታ በሙሉ አቁመዋል።
የዋይት ሀውስ ባለስልጣን ዋሽንግተን ለኪየቭ የሰጠችው በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ዩክሬን ከሩሲያ ሃይሎች ጋር የምታደርገውን ጦርነት ለማስቆም “ለመፍትሄው” ምን ያህል ተጠቅማበታለች የሚለውን እየገመገመች ነው ብለዋል።
አሜሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ትራምፕ ዘለንስኪ ጦርነቱን ለማስቆም ፍላጎት የለውም፣ “የአሜሪካ ድጋፍ እስካለለት ድረስ ሰላምን አይፈልግም” ብለው ከከሰሱ ከሰዓታት በኋላ ነው።
ይህ ውሳኔ ዩክሬን የሩስያን ወረራ ለመመከት በምታደርገው ጥረት ላይ ከባድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል መባሉ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ምላሽ ይስጡ