የዉጫሌ የዉል ስምምነት ለአድዋ ጦርነት መነሻ ምክንያት መሆኑ የሚታወቅ ነዉ፡፡ ይህ ስምምነት የተደረገዉ አምባሳል ወረዳ በተገኘዉ በታሪካዊቷ ዉጫሌ መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን ይህ ቦታ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን እና በአድዋ ታሪክ ያለዉ አበርክቶ ጎልቶ እንዲታይ በማድረግ ዉስጥ በሚገባዉ ያክል አለመሰራቱ ይገለጻል፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን የባህል ቱሪዝም መምሪያ የባህል እሴቶች እና የኢንዱስትሪ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሀይሉ ታደሰ እንደሚሉት በውጫሌ የተካሄደውን ስምምነት ተከትሎ አድዋን መዘከር ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ ስለመሆኑ ያስረዳሉ፡፡ይሁን እንጂ ቦታው ታሪካዊ ኹነቶች የተካሄደበት ቢሆንም ስነ-ምድራዊ አቀማመጡ የበጀት ጥያቄ በመኖሩ ቦታዉን በሚፈለገዉ ልክ ማልማት እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡ የውሉ ስምምነት ለኢትዮጵያዉያንም ሆነ ለመላዉ አፍሪካውያን በጎ እና የአሸናፊነት ተጽእኖን ያሳረፈ በመሆኑ ቦታዉን ከታሪካዊ ድሉ ጋር አብሮ ለማስታወስ በአከባቢዉ ላይ የሙዚየም ግንባታ እየተደረገ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡
ሆኖም በአሁኑ ሰዓት ስፍራው ለቱሪዝም እንቅስቃሴ ነጻ ሆኖ እየተጎበኘ እና መሰራት ያሉባቸው ስራዎች መጠናቀቅ ተችሏል ተብሎ መናገር እንደማይቻልም ነው ያስረዱት፡፡አክለውም በሙዚየሙ ውስጥ የውጫሌ ስምምነት ከመዳሰስ ባለፈ ለአድዋ ጦርነት በቁርሾነት የተቀመጡ አንቀጾችን እና የጦርነቱ ሂደት ከየት እስከ ምን የሚለውንም ማስቃኘት የሚችል እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ቡድን መሪው አክለዉም በአሁኑ ሰዓት የሙዚየሙ ግንባታ መጠናቀቁን የገለጹ ሲሆን ፤ ለሙዚየሙ አስፈላጊ ግብዓቶች ሲሟሉ ለእይታ ክፍት ይሆናል ብለዋል፡፡ የውጫሌ ውል ስምምነት በንጉሥ ምኒሊክ እና በጣሊያን ንጉሥ ኡምቤርቶ ወኪል ኮንት ፔዮትሮ አንቶሎኒ መካከል በአምባሰል ወረዳ ውጫሌ በሚባል ቦታ ሚያዚያ 25 ቀን 1881ዓ.ም የተደረገ ስለመሆኑ የታሪክ ገጾች የሚያስረዱ ሲሆን ውሉ 20 የሚሆኑ አንቀጾችን የያዘ ቢሆንም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳው አንቀጽ 17 መሆኑ ይታወቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ