የካቲት 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮዛሬ ከሌሊቱ 10:35 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ በመኖሪያና ንግድ ቤቶች ላይ አጋጥሞ የነበረዉ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የጸጥታ አካላት የአካባቢዉ ማህበረሰብ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
አደጋ የደረሰበት ቦታና አካባቢ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩ የመኖሪያና የንግድ አካባቢዎች አንዱ ሲሆን ቤቶቹ የተገነቡበት ግብአት የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዉ እንዲሁም የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን አለማስገባቱ ተደማምሮ የእሳት አደጋዉ እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው።
በእሳት አደጋዉ በሰዉና በንብረት ላይ የደረሰዉን ጉዳት እንዲሁም የአደጋዉ መንስዔ ተጣርቶ እንደሚገለጽም ተመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ