በማይናማር ታግተው የነበሩ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ በነበረዉ ጋዜጣዉ መግለጫ ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ መጀመሩን ተናግሯል፡፡በማይናማር ታግተው የነበሩ ዜጎችን ለመመለስ በቅርቡ ዲፕሎማቶች የሚገኙበት ቡድን የተለያዩ መረጃዎችን ለማጥራት ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ቃል አቀባዩ ገልፀዋል፡፡
ቡድኑ የማጥራት ስራ ካከናወነ በኋላ በቀጣይ ሳምንት ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታዉቀዋል፡፡በህገ ወጥ ደላሎች ተታለው ከሀገር የሚወጡ ዜጎችን ለማስመለስ ከበርካታ ሀገራት ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሱዳን የፀጥታ ችግር በመኖሩ አሁን ላይ ሃላፊነት ወስዶ ዜጎችን የሚታደጉበት ሁኔታ አለመኖሩን የገለፁት አምባሳደር ነብያት ከዚህ ቀደም ዜጎችን ከቦታው የማስወጣት ስራ መከናወኑን አስታውሰዋል፡፡
ይህ በእንዲህ አንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ጉብኝት ማድረጋቸው የግንኙነቱ መሻሻል እና በአዲስ መንገድ መጓዝ መጀመሩ ማሳያ ነው ሲሉ ቃል አቀባይ ገልፀዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በአዲስ መንገድ መጓዝ መጀመሩ በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ያመላከተ ነው ብለዋል።
ከሃገራት ጋር ያለ ትብብር አሁንም እንደሚቀጥል ገልጸዉ ፤በቅርቡ የቀድሞው የኤፌደሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በኤርትራ ጉዳይ ላይ በአልጀዚያ ያጋሩት ሀሳብ የመንግስት አቋም አለመሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ