ባለፉት ሰባት ወራት ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ከ3.84 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ወይም የእቅዱን 146% አፈፃፀም ውጤት መገኘቱን ዶክተር ካሣሁን ጎፌ መግለጻቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ለገቢው መገኘት ወርቅ፣ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ኤሌክትሪክ እና የቁም እንስሳት ኤክስፖርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት የእቅዳቸውን ከ100% በላይ አፈጻጸም ማስገኘት የቻሉ የወጪ ንግድ ምርቶች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የሰባት ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው የ1.9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ1.94 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ101.2% ብልጫ እንዳለዉ ዶክተር ካሣሁን መናገራቸው ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ