በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ ልዩ ስሙ አበርጊና ቀበሌ በደረሰ ከፍተኛ የመኪና አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ በ39 ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡
የሰሌዳ ቁጥር ኢት 15591 የሆነ የደረቅ ጭነት መኪና በተለምዶ ካሶኒ እየተባለ የሚጠራ መኪና ከበየዳ ወደ ደባርቅ ከተማ እየመጣ ነበር። የአደጋው ምክንያት የጫነው እህልና ከ50 በላይ ሰዎች በመጫኑ እንደሆነ ይገመታል ተብሏል፡፡ እንዲሁም አሽከርካሪው ለቦታው አዲስ በመሆኑ ሊሆን ይችላል ያሉ ሲሆን በዋነኛነት ግን የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ መምሪያው አስታውቋል።
አሽከርካሪው ለጊዜው አለመያዙም ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ