ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላት እውቅና የጨመረው እና የአውሮፓ ሀያላን ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር በእኩልነት መንፈስ መደራደራቸውን የቀጠሉት ከአድዋ ማግስት መሆኑ ይታወቃል።
አሁን ላይም የአድዋ ገድልን በዲፕሎማሲው መስክ መጠቀም እንደሚገባ የገለጹት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነትና የሠላም ኮሚቴ አባል እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ የፖርላማ ወዳጅነት ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ናቸው።
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በአፍሪካ ህብረት፣ በገለልተኞች ንቅናቄ አስተዋጽኦ ማበርከት የቻለችው በገድሉ በመሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ሊከበር ይገባል ብለዋል።
የአድዋ ድል በዓል በየዓመቱ እንዲከበር በባለቤትነት ኃላፊነት ወስዶ የሚሰራው የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር መሆኑ ይታወቃል፡፡
የዝክረ አድዋ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ አቶ አብርሃም ግዛው፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት፣ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር፤ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሀገራዊ ገፅታ ግንባታ ላይ የሚሰሩ ተቋማት እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ድጋፍ ስላላደረጉልኝ በዓሉን በኪነ-ጥበባዊ ይዘት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ለማክበር ተገድጃለው ብሏል።
የአድዋ ድል የጋራ እንደመሆኑ የአደባባይ በዓል ተደርጎ ዜጎች እንደ ፌስቲቫል እንዲያከብሩት እንዲሁም በክልሎች በመዘዋወር ለመዘከር የተጀመሩ በርካታ ስራዎች መኖራቸውን አዘጋጁ ገልጸዋል።
129ኛውን የአድዋ ድል በዓል ”ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት” በሚል መሪ ቃል በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለማክበር ቅድመ ዝጅቱ መጠናቀቁ በዛሬው ዕለት ተገልጿል።
ምላሽ ይስጡ