በኢትዮጵያ የሚገኙ 13 የመድሃኒት አምራች ፋብሪካዎች የፋይናንስ ችግራቸው ከተፈታ እንደ ሀገር አሁን ላይ ከሚሸፍኑት 30 በመቶ ወደ 60 በመቶ ከፍ እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ አምራቾች ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል፡፡
መድሀኒት አመራቾቹ የፋይናንስ ችግራቸው ከተፈታ ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ወደ ውጭ ሀገራት የሚልኩበት አቅም እንዳለቸው የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳንኤል ዋቅቶሌ ተናግረዋል፡፡
ባንኮች የብድር አገልግሎት ለፋብሪካዎቹ እንዲሰጡ የፖሊሲ ማሻሻያ መደረግ እንዳለበት የማህበሩ ፕሬዝዳንት አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ በበኩላቸው፤ የሀገር ውስጥ የመድሀኒት አምራች ድርጅቶችን የፋይናስ ችግር ለመፍታት ከባንኮች ጋር ዳግም ስምምነት ሊደረግ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
የአምራቾቹን የስራ ማስኬጃ የገንዘብ እጥረት መኖሩን በማንሳት ይህን ችግር ለመፍታት እንደ ተቋም እንዲሁም ሌሎች ይህን የሚደግፉ አካላትን የማሳተፍ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
የመድሃኒት ግብአት ምርት በሀገር ውስጥ አምራቾች እንዲሸፈን እየተደረገ መሆን በመግለፅ የመድሀኒት አቅርቦት በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
ጤና ሚኒስቴር የ2017 የበጀት አመት እቅዱን ባቀረበበት ወቅት ደግሞ በዚህ በጀት ዓመት የሃገር ዉስጥ የመድሃኒት አቅርቦትን አሁን ካለበት 38 ከመቶ ወደ 40 በመቶ የማሳደቅ እቅድ እንዳለዉ መግለጹ አይዘነጋም፡፡
ምላሽ ይስጡ