የአባይ ውሃን በፍትሀዊነት እና በምክንያታዊነት ለመጠቀም ከ15 ዓመት በፊት የተቋቋመ የናይል ቤዚ ኢንሼቲቭ ህጋዊ ቢሆንም ግብፅ ውድቅ ማድረጓዋ እና የናይል ትብብር መድረክ ለቃ ከወጣች 15 አመታት መቆጠሩ ይታወቃል፡፡ የትብብር ጎዳናዎችን ለማምከን ስምምነቱን ያልፈረሙ ሀገራቶች እንዳይፈርሙ ፣የፈረሙም ደግም እንዳያፀድቁ ፣ ያፀደቁትም ለቀው እንዲወጡ ፣ትብብሩ እንዳይቀጥል ፣የገንዘብ ድጋፎች እንዲቆረጡ ከፍተኛ ጥረት ስታደርግ መቆየቷም ይታወቃል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር የውስንነት ተሻጋሪ ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ፈቅ አህመድ የናይል ቤዝ ኢኒሼቲቭን አፍርሶ ወደ ኮሚሽን የመቀየር ሂደት ላይ የግብፅ መመለስ ኮሚሽን እንዳይቋቋም እና ስምምነቶች ወደ ተግባር እንዳይወርዱ ለማድረግ ነው ሲሉ ሀሳባቸውን አንስተዋል።
የዚህ ማሳያው ከቀናት በፊት ሲከበር የነበረው የናይል ቀንን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የተፋሰሱን ሚኒስትሮች ግድቡን እንዲጎበኙ በቀረበዉ ግብዣ ላይ አለመሳተፋ እንደሆነም አመላከተዋል።
የጀርመን መንግስት ግድቡ እንዲጎበኝ የውጪ ልማት ሀገራት ፣አለም ባንክ እና የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች ድጋፍ ቢያደርጉም ግብፅ በመቃወም ጉብኝቱን በማሰረዝ የጀርመን መንግስትን ድጋፍ አቋርጣለች ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የአለም የፖለቲካ አሰላለፍ በጥምረት ወይም በግጭት ነው የሚቀጥለው የሚሉት የፖለቲካል ሳይንስ እና የአለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ እያሱ ሃይለሚካኤል በበኩላቸዉ፤ ግብፅ ወደ ስምምነቱ ለመግባት የሄደችበት እርቀት የራስዋን የብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እንደሆነ አመላክተዋል። የህዳሴው ግድብ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ጥቅሟን ለማስከበር እና ተፅዕኖ ለመፍጠር ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የናይል ትብብርን በተመለከተ ጀማሪ በመሆኗ ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመለወጥ ኮሚሽን በማቋቋም ሂደት ጠንካራ ዲፕሎማሲ ስራ መስራት እንዳለባት ባለሙያዎቹ አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ