ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚውል 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱ ተመላክቷል።
ከዚህ ውስጥ 614 ሺህ 865 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን እስከ የካቲት 16/2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተመላክቷል።
በጅቡቲ ወደብ 12 መርከቦች ላይ 640ሺህ 795 ነጥብ 1 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ተጭኖ መድረሱ ተመላክቷል። ከዚህ ውስጥ 614ሺህ 865 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው ማዳበሪያ ውስጥ 90ሺህ 965 ሜትሪክ ቶን በባቡር፣ 523 ሺህ 900 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች መጓጓዙን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ምላሽ ይስጡ