ኢሮፕያን ሳተላይት ባወጣው መረጃ በፈንታሌ ወረዳ ከወራት በፊት ሲከሰት የነበረውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ባልተለመደ መልኩ ሚቴን የተሰኘ የተፈጥሮ ጋዝ መገኘቱን ዘግቧል።
እንዲሁም በተፈጥሮ ጋዝ ዙሪያ የሚሰራው ጂ.ኤች.ጋስት የተሰኘው የካናዳ ድርጅት እንደገለፀው፤ በአሁኑ ሰዓት በተራራው በቀን 1ሺሕ 400 ቶን የሚገመት ጋዝ እየወጣ መሆኑንም ገልጿል።
ይንን መረጃ መነሻ በማድረግ መናኸሪያ ሬዲዮ የማዕድን ሚኒስቴርን ስለ ጉዳዩ ጠይቋል።
የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፤ ተገኘ ስለተባለው የሚቴን ጋዝ ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከማዕድን ሚኒስቴር የጂኦሎጂ ኢንስቲትዩት እና ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተወጣጡ ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮሚቴ በማዋቀር ቦታው ድረስ ጥናት እንዲያደርጉ መላካቸውን ገልፀዋል።
በጥናቱ የጋዙን ትክክለኛነት፣ በቀን ምን ያህል እየወጣ እንደሆነ፤ የክምችቱ ቀጣይነት እንደሚረጋገጥ ነው ሚኒስትር ዴኤታው ያስታወቁት።
የጥናቱ መጠናቀቅን ተከትሎ ዝርዝር መረጃ ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል።
ምላሽ ይስጡ